2024 Guests Of Honor

Each year, ESFNA invites individuals that have excelled in sports in Ethiopia in the past. From soccer players to long distance runners that have made the proud nation even prouder. Besides sports figures, ESFNA also honors Ethiopians in the social and art field. If it were not for the invitation of ESFNA, most of these heroes would not have had the opportunity to visit the United States.

መቶ አለቃ በሀብቱ ገብረማሪያም

የክብር እንግዳ

ትውልዱ መርካቶ ቁጭራ ሠፈር ነው ።ከልጅነቱ አንስቶ በውስጡ የተፈጠረው እግር ኳሰኛ የመሆን ስሜት ሁሉንም ነገር አሸንፎ ታዋቂው ብስክሌተኛ ገረመው ደንቦባ ያቋቋመው እግር ኳስ ቡድን ዘርዐይ ደረስ በመቀላቀል የእግር ኳስ ህይወቱን መኖር ጀመረ። ታዋቂው እግር ኳሰኛ በሀብቱ ገ/ማርያም በ41ኛው አመት የፌደሬሽናችን የክብር እንግዳ በመሆን የተመረጠው በክለብ ደረጃ ለቀድሞው የመቻል ቡድን እና ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በመጫወት ታላቅ ገድልን ፈፅሟል።

ዘንድሮ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ የ41ኛ ዓመቱን በሚያከብርበት ወቅት የክብር ዕንግዳ ሆነህ በመመረጥህ ምን ተሠማህ ያልነው በሀብቱ እንባ ቀደመው:: ከእኔ የበለጠ ስራ የሠሩ ብዙዎች ቢኖሩም በጣም ደስ ብሎኛል ሲል በዕንባ የታጀበ መልስ ሠጥቷል።በ1949 የተወለደው በሀብቱ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርቱን በደጃዝማች ዑመር ሠመተር ት/ቤት ተከታትሏል።

በ1963 እናት ሀገሩን ለማገልገል ጦሩን የተቀላቀለው በሀብቱ ከ1967 እስከ 1978 መቻል ክለብ እንዲጫወት በር ተከፈተለት:: በሀብቱ በመቻል ቆይታው ድንቅ አጥቂ የነበረ ሲሆን የጭንቅላት ጎሎችን በማስቆጠር የወቅቱ ወደር አልባ እንደነበር ታሪክ ያወሳዋል።

በሀብቱ ከመቻል ጋር በነበረው ቆይታ በ1968 እና 1976 በተጫዋችነት እንዲሁም በ1981 በአሠልጣኝነት የኢትዮጵያ ሻምፒየን መሆን ችሏል።
በሀብቱ ገ/ማርያም የሚለው ስም ሲነሳ አስቂኝ የሽልማት ገጠመኙ በብዙሀኑ ህሊና ይከሠታል:: ነገሩ እንዲህ ነው በ1976 የኮከብ ግብ አግቢነት ሽልማት ሲጀመር ከ3 ተሸላሚ ኮከቦች መካከል አንዱ እርሱ ነበር እናም ሸራ ጫማ ይሸለማል:: እቤቱ ገብቶ ሽልማቱን አድርጎ ለመዘነጥ ሲለካው አንድ እግሩ 43 ሌላኛው 44 ቁጥር ሆኖ አስገራሚ ገጠመኝን ፈጥሯል። ያን ሸራ ጫማ በታሪክ እንዲቀመጥ ሻምበል አበበ ቢቂላ ስፖርት ቤት ማድረጉንም በሀብቱ በፈገግታ ታጅቦ ያወሳል።

በብሄራዊ ቡድን ደረጃም ከ1970 አንስቶ ለ7 ዐመታት ቡድኑን አገልግሏል። በጨዋታ ሜዳ ምስጉን የነበረው በሀብቱ በተጫዋችነት ዘመኑ አንድም ቀይ ካርድ አልተመለከተም።

በአሠልጣኝነቱም የካፍ ኤ ላይሠንስ ያለው ሲሆን መቻል እና መድንን ወደ ፕ.ሊጉ ማሣደግ ችሏል። ሌሎች ክለቦችንም በስኬት አሠልጥኗል።
ላለፉት 40 ዐመታት በኢትዮጵያ እግር ኳስ ትልቅ አሻራውን ያኖረው በሀብቱ ገ/ማርያምን የክብር ዕንግዳ አድርገን በመጋበዛችን ፌደሬሽኑ ትልቅ ክብር ይሠማዋል።

በሀገረ አሜሪካ እና አውሮፓ የሚገኙ የቀድሞ እግር ኳሰኞች በሀገር ውስጥ ለሚኖሩ የቀድሞ ጓደኞቻቸው ድጋፍ ሲያደርጉ ያስተባብራል። በአ.አ እግር ኳስ ፌደሬሽን ውስጥም በተለያዩ ሀላፊነቶች ያገለገለው በሀብቱ በዚህ ታላቅ እና አምሣለ ኢትዮጵያ በሆነው ፌደሬሽን የክብር ዕንግዳ ሆኜ በመመረጤ ይህን ላደረጉ ሁሉ ክብር ይሁንልኝ ብሏል።

ናዖሚ ግርማ

ልዩ የክብር እንግዳ

በአሜሪካ የሴቶች አግር ኳስ ታሪክ በአጭር ግዜ ጉዞ ስኬታማነትን ከተጎናፀፉ እንስቶች አንዷ ናኦሚ ግርማ ናት። በሳን ሆዜ ካሊፎርኒያ ከኢትዮጵያውያን ወላጆች የተገኘችው ናኦሚ በጎርጎሮሳዊው የዘመን ቀመር በ2022 በአሜሪካ የሴቶች ብሄራዊ ሊግ የአመቱ ምርጥ ተከላካይ ተብላ ተመርጣለች። ባለፈው 2023 ከሀገርዋ ብሄራዊ ቡድን ጋር በአለም ዋንጫ የተሣተፈች ሲሆን በዚሁ አመት የአሜሪካ የአመቱ ምርጥ እንስት እግር ኳሰኛ የሚል ሽልማትን አግኝታለች።

የናኦሚ በስኬት ያሸበረቀ የእግር ኳስ ህይወቷ የሚጀምረው አቧቷ ባቋቋመው የእግር ኳስ አነስተኛ ፕሮጀክት ነው:: ማለዳ የሚል ስያሜ የተሠጠው ይህ ፕሮጀክት በ2005 ሲቋቋም ናኦሚ እና መሠል በእግር ኳስ የተነኩ ታዳጊዎችን በመያዝ ነበር። ከዚያም ናኦሚ በት/ቤት የወንድሟን ፈለግ በመከተል የተለያዩ ስፖርቶች ላይ ተሣትፎ ታደርግ ነበር ለ5 አመታት ጅምናስቲክ ስፖርት ላይ የቆየችው ናኦሚ መካከለኛ ክፍል ስትገባ ሙሉ ትኩረቷን እግር ኳስ ላይ አደረገች።
ናኦሚ እና ህልሟ ተገናኙ
በ2009 በአካባቢው በሚገኝ ቡድን እንድትጫወት ናኦሚ በጓደኛዋ ግብዣ ተደረገላት በወቅቱ ቡድኑን ሲያሠለጥን የነበረው ቦብ ጆይስ በልጅቱ ብቃት ተገረመ ደጋግማ እንድትመጣ ፈቀደላት በክሮስ ፋየር ቡድን እስከ 2017 ቆይታ ያደረገችው ናኦሚ ወደ ኦሎሚፒክ ዴቨሎፕመንት ፕሮግራም በመግባት እንድትሠለጥን አሠልጣኟ ያበረታታት ነበር።
በኮሌጅ ቆይታዋ የስታንፎርድ ካርዲናል ቡድንን በአምበልነትየመራች ሲሆን እሷ አምበል ሆና በ2019 ቡድኗ የኮሌጆች ሻምፒዮን ሆኗል።

ናኦሚ ፕሮፌሽናል የክለብ ህይወቷ የሚጀምረው በሳንዲዬጎ ኤፍ ሲ ነው በ2022 ቡድኑን የተቀላቀለችው ናኦሚ በግንቦትእና ሰኔ የሀገሪቱ ምርጥ 11 ስብስብ ውስጥ በመካተት ጉዞዋን የበለጠ የሠመረ ማድረግ ችላለች። በዛው አመት ምርጧ የወሩ ተጫዋች ሰኔ ላይ እንዲሁም የአመቱ ምርጧ ተከላካይ ክብርን ወስዳለች። እያሣየች ባለው ድንቅ ብቃት በበርካታ የአውሮፓ ክለቦች አይን ውስጥ ብትገባም ክለቧ እስከ 2026 ኮንትራቷን አራዝሟል።

2023 እና የናኦሚ ዘርፈ ብዙ ስኬት አመቱ ከኢትዮጵያውያን ቤተሠብ ለተገኘችው ናኦሚ ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ ለመላው ኢትዮጵያዊያን አስደሣች ነበር:: በዚህ አመት አውስትራሊያ እና ኒውዝላንድ በደገሱት የአለም ዋንጫ ቋሚ ተሠላፊ በመሆን ለአሜሪካ ብሄራዊ ቡድን በጥሩ ብቃት ተጫውታለች። በዚሁ አመት በአሜሪካ ብሄራዊ የሴቶች ሊግ የ39 ዐመት ታሪክ ሁለተኛዋ ጥቁር የመጀመሪያዋ የተከላካይ መስመር ተጫዋች ሆና የአመቱ የአሜሪካ ምርጥ እግር ኳሰኛ የሚለውን ክብር ተቀዳጅታለች።

ከ17 ዐመት በታች አንስቶ የአሜሪካ ቡድን የተጫወተችው ናኦሚ የ20 ዐመት በታች ቡድኑን እየመራች የኮንካፍ ዋንጫን አንስታለች።በላውራ ሀርቬይ ይሰለጥን በነበረው ቡድን ባሳየችው ድንቅ ብቃት የአመቱ ምርጥ ወጣት እግር ኳሰኛ ተብላ በ2020 ተመርጣም ነበር።

የአቶ ግርማ አወቀ እና የወ/ሮ ሰብለ ደምሴ ልጅ የናትናኤል የ3 ዐመት ታናሽ እህት የሆነችው ናኦሚ ግርማ አሁንም በእግር ኳሱ የበለጠ ስኬት ታገኝ ዘንድ ምኞታችን ነው። ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን በተሠማሩበት መስክ ስኬታማነታቸው ከፍ ብሎ ለሀገር ብሎም ለወገን ኩራት ሲሆኑ መመልከት የፌዴሬሽናችን ደስታ ነው።

Dignitaries

ESFNA is honored to welcome distinguished dignitaries to our events. These prominent individuals represent various spheres of influence and contribute to the growth and prosperity of Ethiopian-American communities in North America. We invite esteemed government officials, renowned business leaders, accomplished academics, and influential community advocates. Their presence adds prestige and significance to our gatherings, fostering a spirit of unity and empowerment among Ethiopians in the diaspora. ESFNA is proud to provide a platform for these distinguished guests to connect, collaborate, and inspire positive change within our community.

Previous Dignitaries

Rep. Maxine Waters

Rep. Mike Honda

Rep. John Lewis

Rep. Karen Bass

Isiah Leggett

Mayor Sam Liccardo

ESFNA’s Early Years

Preloader
  • DR. AKILIU HABTE

    DR. AKILIU HABTE

  • MENGISTU WORKU

  • TESFAYE SEYOUM

  • YIDNEKACHEW TESSEMA & YEHARERWERK GASHAW

    YIDNEKACHEW TESSEMA & YEHARERWERK GASHAW

  • MAMO WOLDE

  • ADAMU ALEMU

  • GETACHEW ABEBE (DULA)

  • LUCIANO VASSALO & ITALO VASSALO

  • KEBEDE METAFARIA & DERARTU TULU

    KEBEDE METAFARIA & DERARTU TULU

  • AWAD MOHAMMED & LAURATE TSEGAYE GEBRE MEDHIN

    AWAD MOHAMMED & LAURATE TSEGAYE GEBRE MEDHIN

    The legendary Poet Laureate, playwright, essayist, and art director.

  • GETACHEW WOLDE & KAGNEW KITACHEW

  • TADESSE G/MEDHIN & SEIDO ABDELLA

  • MIRUTS YIFTER

    MIRUTS YIFTER

  • FEKADE MULETA

  • PROFESSOR ASRAT WOLDEYES

  • NEGUSIE GEBRE

  • GEREMEW ZERGAW & ZEWDE SAMUEL

  • MOHAMMED HUSSEIN AL-AMOUDI & WAMI BIRATU & ASRAT HAILE

  • ENGDAWORK TARIKU & TEKA GEBRETSADIK

  • ALEMAYEHU HAILE SELASSIE & ABDURAHAMN ADEM & HAYAT AHMED

  • SEYOUM ABATE & DEMISSIE DAMTE & HAILE GEBRE SELASSIE

    SEYOUM ABATE & DEMISSIE DAMTE & HAILE GEBRE SELASSIE

  • GEREMEWU DEMOBOBA & FISSEHA W/AMMANUEL & TILAHUN GESSESSE & DR. RICHARD PANKHURST

    GEREMEWU DEMOBOBA & FISSEHA W/AMMANUEL & TILAHUN GESSESSE & DR. RICHARD PANKHURST

  • MAITER AFEWERK TEKLE & KASSAHUN TEKA & YILMA KETEMA

  • BASHA HAILU ABEBE & MULATU ASTATKE

    BASHA HAILU ABEBE & MULATU ASTATKE

  • ASFAW KEBEDE & YAREGAL G. YESUS

  • WONDIMU BEKELE & MAHARI TAYE & JUDGE BIRTUKAN MIDEKSA

    WONDIMU BEKELE & MAHARI TAYE & JUDGE BIRTUKAN MIDEKSA

  • TESFAYE SHIFERAW

  • AREFAYNE MITIKU

  • TESFAYE FETENE

  • ASCHALEW DESSIE

Share This